በአማራ ክልል ከተሞችን በማልማትና ዲጂታላይዝድ በማድረግ የኢኮኖሚ ምንጭ እንዲሆኑ እየተሰራ ነው – ዶክተር አህመዲን መሐመድ

በአማራ ክልል ከተሞችን በማልማትና ዲጂታላይዝድ በማድረግ የኢኮኖሚ ምንጭ እንዲሆኑ እየተሰራ ነው – ዶክተር አህመዲን መሐመድ

በአማራ ክልል ከተሞችን በማልማትና ዲጂታላይዝድ በማድረግ የኢኮኖሚ ምንጭ እንዲሆኑ እየተሰራ መሆኑን በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የከተሞች ልማት ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ከተሞችና መሰረተ ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር አህመዲን መሐመድ ገለጹ።

የአማራ ክልል ከተሞችና መሰረት ልማት ቢሮ የከተሞች ተቋማዊና መሰረት ልማት ማስፋፊያ ፕሮግራም እቅድ አፈጻጸም ማጠቃለያ መድረክ በደሴ ከተማ እየተካሄደ ነው።

በመድረኩ ላይ ዶክተር አህመዲን መሐመ እንዳመለከቱት፤ በከተሞች መሰረተ ልማትን ተደራሽ በማድረግ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተሰራ ይገኛል።

ለስራ ፈላጊዎች የስራ እድል መፍጠርን ጨምሮ ሌሎችንም ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ለማሳደግ ከተሞችን ማልማትና ዲጂታላይዝድ የማድረግ ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

ከተሞችን በማልማትና በቴክኖሎጂ በማበልጸግ የኢኮኖሚ ምንጭ ጭምር እንዲሆኑ ትኩረት መሰጠቱን ተናግረዋል።

በተለይ በከተሞች መሰረት ልማት መገንባት፣ ቴክኖሎጂንና ኢንዱስትሪን እዲ አረንጓዴ ልማትን ማስፋፋት እንደሚገባ ገልጸዋል።

በዚህም ለሰዎች የስራ እድል መፍጠር፣ ብልሹ አሰራርን መከላከል፣ ኑሮውን ማረጋጋት፣ አገልግሎትን ማሻሻልና ማዘመን ይገባል ብለዋል።

ፕሮግራሙ በክልሉ 32 ከተሞች ላይ ሲተገበር እንደቆየ ጠቁመው፤ ህብረተሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የተለያዩ የልማት ስራዎች መከናወናቸውን አብራርተዋል።

በፕሮግራሙ በ15 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር በጀት 3ሺህ 885 የተለያዩ ፕሮጀክቶች እየተሰሩ መሆናቸውንና አፈጻጸማቸውም 91 በመቶ መድረሱን በመድረኩ ከቀረው ሪር መረዳት ተችሏል።

በጀቱም የመንግስት፣ የዓለም ባንክና የህብረተሰቡ ድጋፍ መሆኑም ተመልክቷል።

ከስራዎቹ መካከል አስፋልትና የድንጋይ ንጣፍ መንገድ፣ የአቅመ ደካሞች መኖሪያ ቤትና የስራ እድል መፍጠሪያ ሼድ እንደሚገኙበት ተጠቅሷል።

የደሴ ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ በፕሮግራሙ ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ያደረጉ ሰፋፊ መሰረተ ልማቶች ማከናወን መቻሉን ገልጸዋል።

ከእነዚህም መካከል የአስፋልት ንገድ ጠና ለአገልግሎት መብቃቱን ተናግረዋል።

በመድረኩ የፕሮግራሙ ከ2011 ዓ.ም እስከ 2015 ዓ.ም እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት እየቀረበ ሲሆን፤ ውይይት ተደርጎበት አቅጣጫ ይቀመጣል ተብሎም ይጠበቃል።

በመድረኩ የክልል፣ የዞንና የከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራር አባላትና ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል።

Dive into the world of Cash Prizes and Contests, offering real cash rewards for participation in various games and challenges.

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top