“ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ለማምጣት ከተሞችን የዕውቀት ማዕከል ማድረግ ይገባል” አሕመዲን ሙሐመድ (ዶ.ር)

“ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ለማምጣት ከተሞችን የዕውቀት ማዕከል ማድረግ ይገባል” አሕመዲን ሙሐመድ (ዶ.ር)

ደሴ: ሐምሌ 18/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል የከተሞች እና መሠረተ ልማት ቢሮ የከተሞች ተቋማዊ እና መሠረተ ልማት ማስፋፊያ ፕሮግራም ከ2011 እስከ 2015 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ማጠቃለያ የውይይት መድረክ በደሴ ከተማ አካሂዷል።

ፕሮግራሙ በክልሉ 32 ከተሞችን አቅፎ ባለፉት አምስት ዓመታት ሲካሄድ ቆይቷል፡፡ በቆይታውም በከተሞች የመሠረተ ልማት እና በተቋማት የግንባታ ሥራ ሠርቷል።

ለፕሮግራሙ ማስፈጸሚያ ከ15 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት መመደቡን እና በአምስት ዓመታት ውስጥ ከ250ሺህ በላይ ለሚኾኑ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር መቻሉ በመድረኩ ላይ ተነስቷል።

በጦርነት ምክንያት ጉዳት ከደረሰባቸው ከተሞች ውጭ አብዛኞቹ በፕሮግራሙ የታቀፉ ከተሞች አማካኝ የገቢ ዕድገታቸው ከ20 በመቶ በላይ መኾኑም ተገልጿል።

የደሴ ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ሳሙኤል ሞላልኝ በደሴ ከተማ የተጀመረው የከንቲባ ችሎት የከተማዋ ነዋሪዎች ቅሬታ የተመለሰበት እንደኾነ ገልጸዋል፡፡ ለረዥም ጊዜ ሲጠየቁ የቆዩ የመልማት ጥያቄዎች የተመለሱበት ፕሮግራም መኾኑንም ነው ያስገነዘቡት፡፡

የደቡብ ወሎ ዞን ዋና አሥተዳዳሪ አሊ መኮነን በዞኑ የፀጥታ ኀይሉን በማጠናከር እና ሰላሙን በማረጋገጥ በኩል ውጤታማ ሥራ እንደተሠራ ተናግረዋል።

የመንገድ መሠረተ ልማት ሥራዎችን በመሥራት የኅብረተሰቡን ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ከፍ ማድረግ መቻሉን ዋና አሥተዳዳሪው ገልጸዋል።

በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የከተሞች ልማት ዘርፍ አስተባባሪ እና የከተማ እና መሰረተ ልማት ቢሮ ኀላፊ አሕመዲን ሙሐመድ (ዶ.ር) በክልሉ ኢንዱስትሪዎችን እና መሠረተ ልማቶችን ማስፋፋት እንዲሁም ዲጂታል ትራንስፎርሜሽ በከተሞች መተግበር ይገባል ብለዋል፡፡

ዶክተር አሕመዲን ሙሐመድ “ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ለማምጣት ከተሞችን የዕውቀት ማዕከል ማድረግ ይገባል” ነው ያሉት፡፡

ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን፣ የመሰረተ ልማት ሥራዎች፣ ኢንዱስትሪዎችን ማስፋፋት፣ ከተሞችን የዕውቀት ማእከል ማድረግ እና ከተሞች የሚሠሯቸው የልማት ሥራዎችን ከአረንጓዴ ልማት ማስተሳሰር የከተማ እና መሰረተ ልማት ሥራዎች የትኩረት አቅጣጫዎች ናቸው ብለዋል።

ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ላይ ትኩረት ሰጥቶ በመሥራት የተገልጋን እርካታ ማረጋገጥ፣ የሥራ አጥ ቁጥርን መቀነስ እንዲሁም ከተሞች የጀመሩትን የልማት ሥራዎችን ማስቀጠል ይገባል ነው ያሉት።

በመሰረተ ልማት ዘርፍ የቤት አቅርቦት ላይ በትኩረት በመሥራት የመንግሥት ሠራተኞችንና ሌሎችንም የኅብረተሰብ ክፍሎች የቤት ባለቤት ማድረግ ይገባል ብለዋል።

ዶክተር አሕመዲን በክልሉ ያሉ ፀጋዎችን በመጠቀምና አቅምን አሟጦ በመጠቀም ኢንዱስትሪዎችን ማስፋፋት ይገባል ነው ያሉት።

በትምህርት ዘርፍ ኢንፎርሜሽንና ቴክኖሎጂን ማሳደግና ከተሞችን የዕውቀት ማእል ማድረግ እንደሚገባም ነው ዶክተር አሕመዲን ያሳሰቡት።

በከተሞች የሚሠሩ የልማት ሥራዎች ከአረንጓዴ ልማት ጋር ማያያዝ እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

ባለፉት ዓመታት የተከሰተው ግጭት፣ የግንባታ ግብዓቶች እጥረት እና ዋጋ መናር በፕሮግራሙ ትግበራ ሂደት ላይ እክል መፍጠሩ ተመላክቷል፡፡

በውይይት መድረኩ የፕሮግራሙ ተጠቃሚ ከተሞች ከንቲባዎች፣ የክልል ቢሮ ኀላፊዎች እና የሚመለከታቸው ባለሙያዎች ተገኝተዋል፡፡

모바일 카지노 게임에 대한 모든 것을 알아보려면 여기를 방문하세요.

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top