“የባሕር ዳር ስታዲየም ትልልቅ መሠረተ ልማቶችን የያዘ ታላቅ የሕዝብ ሃብት ነው” የአማራ ክልል ቤት አባላት
በአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ የተመራ የአማራ ክልል ምክር ቤት ቡድን የባሕር ዳር ስታዲየምን ጎብኝቷል።
በጉብኝቱ የተገኙ የቋሚ ኮሚቴ ሠብሣቢዎች እና የቋሚ ኮሚቴ አባላቱ የባሕር ዳር ስታዲየም የሥራ እንቅስቃሴ የሚደነቅ መኾኑን ገልጸዋል።
የሴቶች ሕጻናት እና ማኅበራዊ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ አባል ሩት አስፋው የባሕር ዳር ስታዲየም በተሻለ ፍጥነት እየተሠራ መኾኑን መመልከታቸውን ተናግረዋል።
ባር ር ስታዲየም ዘግይቷል በሚል በቋሚ ኮሚቴው በተደጋጋሚ ይገመገም እንደነበር ያስታወሱት ወይዘሮ ሩት በቦታው ተገኝተው በተግባር ሲያዩት ግን የተሻለ እንቅስቃሴ ማግኘታቸውን ገልጸዋል።
ስታዲየሙን ለመጨረስ የሚደረውገውን ርብርብ የበለጠ አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባም አመላክተዋል። ቋሚ ኮሚቴው የሥራውን እንቅስቃሴ ክትትል እያደረገ በፍጥነት እንዲጠናቀቅ እንደሚሠራም ገልጸዋል።
የሰው ሃብት እና ቱሪዝም ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባል ደምስ እንድሪስ የባሕር ዳር ስታዲየም በቶሎ ተጠናቅቆ ለአገልግሎት ክፍት እንዲኾን ሲየቅ ቆየን ተናግረዋል።
ስታዲየሙ አሁን ላይ በጥሩ የሥራ እንቅስቃሴ ላይ መኾኑን መመልከታቸውንም አስታውቀዋል። ሥራው በፍጥነት እና በጥራት እየተከናወነ መኾኑን ተመልከተናልም ብለዋል። ባዩት ነገር መደሰታቸውንም ነግረውናል።
ስታዲየሙ በፍጥነት ተጠናቅቆ እና ለአገልግሎት ክፍት ኾኖ በሌሎች አካባቢዎችም ስታዲየሞች እንዲገነቡ እንፈልጋለንም ብለዋል። ቋሚ ኮሚቴውም አስፈላጊውን ድጋፍ እና ክትትል ያደርጋል ነው ያሉት።
የበጀት እና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባል አሊ ይማም ታዲየ ዓለም አቀ ጠብቆ እየተሠራ መኾኑን ተመልከተናል ብለዋል። በርካታ ሥራዎች በውስጡ እየተሠሩ መኾናቸውንም ገልጸዋል።
ምክር ቤቱ የሚበጀተውን በጀት አስፈጻሚው አካል ለታለመለት ዓላማ እያዋለ እንደኾነ አረጋግጠናልም ብለዋል። ያልተጠናቀቁ ሥራዎችንም ቁጥጥር እና ክትትል እያደረጉ ማጠናቀቅ ይገባል ነው ያሉት።
መንግሥት ከሚበጅተው በጀት በተጨማሪ ባለድርሻ አካላትም መሳተፍ እንደሚጠበቅባቸውም አመላክተዋል።
የሰው ሃብት እና የቱሪዝም ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሠሣቢ አበሽ ታደሰ የስዲሙ ሥ አፈጻጸም በጥሩ ደረጃ ላይ መኾኑን ገልጸዋል። በመስክ ምልከታቸው በርካታ ለውጦችን መመልከታቸውንም ተናግረዋል።
ስታዲየሙ ለሥራ ከወሰደው የጊዜ እርዝመት አንጻር ማኅበረሰቡ የት ደረሰ እያለ እንደሚጠይቅ እና አሁን ላይ በጥሩ ሂደት ላይ መኾኑን ገልጸዋል።
ስታዲየሙ ካለፉት ጊዜያት አንጻር በጥሩ ለውጥ ላይ መኾኑን የተናገሩት ሠብሣቢዋ የክልሉ መንግሥት ልዩ ትኩረት እንደሰጠውም ተናግረዋል።
የስታዲየሙን የግንባታ ሂደት የሚከታተሉ መሪዎችም በዕውቀት ላይ መሥርተው እንደሚመሩት ታበና ነ ያሉት። ለስታዲየሙ ግንባታ ማጠናቀቂያ በጀት መመደብ፣ ክትትል እና ድጋፍ ማድረግ ከምክር ቤቱ እንደሚጠበቅ ተናግረዋል።
የሕግ ፍትሕ እና አሥተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሠብሣቢ ደሴ ጥላሁን (ዶ.ር) ቋሚ ኮሚቴው የተቋማትን አፈጻጸም በገመገመበት ወቅት ትኩረት ሰጥቶ ከገመገማቸው ጉዳዮች አንደኛው የባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም አንዱ እንደነበር አስታውሰዋል።
የምክር ቤት አባላቱ አፈጻጸሙ ያለበትን ደረጃ፣ የካፍ እና የፊፋ ደረጃዎችንም ጠብቆ እየተገነባ ነው ወይ የሚል ተደጋጋሚ ጥያቄ ተነስቶት እንደነበም ገልጸዋል።
በጉብኝታቸው ሲነሱ የነበሩ ጥያቄዎችን በተግባር ተመልሰው ማየታቸውንም ተናግረዋል። የካፍ ደረጃዎችን በሚያሟላ መልኩ እየተሠራ መኾኑን ማብራሪያ እንደተሰጣቸው እና በተግባርም ማየታቸውን ነው የገለጹት። ማኅበረሰቡ እና ቋሚ ኮሚቴው በስፋት ጥያቄ የሚያነሳበት ፕሮጀክት በሥራ ላይ መኾኑንም አይተናል ነው ያሉት።
እየተሠራ ባለው ሥራ ደስተኛ መኾናቸውን የተናገሩት ሠብሣቢው ትልልቅ መሠረተ ልማቶችን የያዘ ታላቅ የሕዝብ ሃብት ነው ብለዋል።
የሕዝብ ሃብት ለነው ስታዲየም ትኩረ መሥት እንደሚገባም መላ ሌሎች የክልሉ አካባቢዎች የስፖርት ልማት ሥራዎች እንዲሠሩ ትኩረት እንደሚደረግም አንስተዋል።
የባሕር ዳር ስታዲየምን በፍጥነት ማጠናቀቅ ከስታዲየሙ የሚገኘው ገቢ ሌሎች ልማቶች እንዲለሙ ያደርጋል ነው ያሉት። የፕሮጀክት አሥተዳደር ክፍተት እንዳይኖር ቁጥጥር ማድረግ እንደሚገባም ገልጸዋል። የተጀመሩ ፕሮጀክቶች በፍጥነት መጠናቀቅ አለባቸውም ብለዋል።
የሴቶች ሕጻናት እና ማኅበራዊ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ሠብሣቢ እመቤት ከበደ በስታዲየሙ በርካታ የማስፋፊያ ሥራች እየተሠሩ መመልከታቸን ገልጸል። ዘመናዊነትን የላበ ሥራዎ እየተሠሩ መኾናቸውንም ተናግረዋል። ስታዲየሙ ከተጀመረ ረጅም ዓመታት በማስቆጠሩ ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እንደሚነሱበትም ገልጸዋል።
ከሕዝብ ፍላጎት አንጻር በፍጥነት መጠናቀቅ ይገባዋልም ብለዋል። ስታዲዬሙ በተባለው ልክ እንዲጠናቀቅ የሚጠበቅባቸውን ድጋፍ እንደሚያደርጉም አስታውቀዋል።
Benefit from Instant Withdrawal Bonuses, rewarding players who use specific payment methods for fast cashouts.