የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም
በአዲስ አበባ ከተማ
የዓድዋ ድል የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ/ም ኢትዮጵያ በጀግኖች ልጆቿ ወራሪውን የጣሊያን ሰራዊት ያሸነፈችበት ወርቃማ ድል ነው።
በአስደናቂ የአመራር ጥበብ ኢትዮጵያዊያን በአንድነትና በቆራጥነት ተሰልፈው በጣሊያን ላይ ያስመዘገቡት ድል ለኢትዮጵያና ለሕዝቧ ዓለምአቀፍ እውቅናን ያጎናፀፈ፤ የቅኝ ገዥዋችን ቅስም የሰበረ፤ በመላው ዓለም የሚገኙ ጥቁር ሕዝቦች ለነጻነታቸው እንዲነሱ ያነቃቃ ድል ነው፡፡
ይሄን ትርጉመ ብዙ የሆነ ድል ኢትዮጵያ ከዳግማዊ ምኒልክ ዘመን መንግስት ወይም 1895 ዓ/ም ጀምሮ በብሔራዊ ደረጃ እያሰበችውና እያከበረችው ትገኛለች።
የድል በዓሉን ለማዘከርም በዓሉ ለመጀመሪያ ጊዜ በተከበረበት አራዳ ጊዮርጊስ አደባባይ ንግሥተ ነገሥት ዘውዲቱ የዓድዋ ድል መሪ ለሆኑት ዳግማዊ ምኒልክ የመታሰቢያ ሐውልት አሰርታለች።
ከ128 ዓመታት በኋላ ደግሞ ከመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን እና ዳግማዊ ምኒልክ አደባባይ ትይዩ የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም እጅግ አስደናቂ በ መንገድ ተሰርቶ ለሕዝብ ክፍት ተደርጓል።
የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ታላቁን የዓድዋ ድል ታሪክ በሚመጥን እና ትውልድ ተሻጋሪ ሆኖ 3.3 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ ድንቅ ሙዚየም ነው። በውስጡም የዳግማዊ ምኒልክና እቴጌ ጣይቱ እንዲሁም የዓድዋ ጦር መሪዎች ሐውልት፣ የዓድዋ የታሪክ አሻራዎች፣ የዓድዋ 00 መነሻ፣ ፈረሰኞችን፣ የዓድዋ ድል ማክበሪያ ቦታ፣ የአትክልት ስፍራ፣ 1000 መኪና ማስተናገድ የሚችል የመኪና ማቆሚያ፣ ተጨማሪ ሁለት ስማርት የመኪና ማቆሚያዎች፣ 2000 ሰው ማስተናገድ የሚችል ትልቅ አዳራሽ፣ ከ160-260 ሰው የሚያስተናግዱ 3 ትንንሽ አዳራሾች፣ የቤት ውስጥ ስፖርታዊ ውድድች ማ የሚችል አዳራሽ፣ የሕፃናት መጫወቻ፣ ጅምናዚየም፣ ሲኒማ ቤት፣ አንፊ ቲያትር እና ግዙፍ ሬስቶራንት ይዟል።
በዋና አርክቴክት እስክንድር ውበቱ ውብ ሆኖ የተሰራው ሙዚየሙ በአራቱም አቅጣጫዎች ወደ ዓድዋ የተመመውን ሕዝብ ለመወከል አራት ዋና መግቢያዎችን ማለትም፦
1 ) የሰሜን ጀግኖች በር
2) የምሥራቅ ጀግኖች በር
3) የደቡብ ጀግኖች በር
4) የምዕራብ ጀግኖች በር በማለት ሰይሟል። ከናዎ በሮች ተማ እ ቪአይፒ በር የመሳሰሉ ሌሎች በሮችም በሙዚየሙ የተለያየ አቅጣጫ ይገኛሉ።
በዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ለንጉሠ ነገሥት ዳግማዊ ምኒልክ እና እቴጌ ጣይቱ እንዲሁም ለሚከተሉት 12 ዋና የዓድዋ ጦር መሪዎች የመታሰቢያ ሐውልት ቁሞላቸዋል።
1) ንጉሥ ተ/ሐይማኖት (አባ ጠና)
2) ንጉሥ ሚካኤል (አባ ሻንቆ)
3) ራስ አባተ ቧያለው (አባ ይትረፍ)
4) ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም (አባ ድብ)
5) ፊታውራሪ ገበየሁ (አባ ጎራው)
6) ልዑል ራስ መኮንን (አባ ቃኘው)
7) ራስ መንገሻ ዮሐንስ (አባ ግጠም)
ደጃዝማች ባልቻ (አባ ነፍሶ)
9) ራስ ወሌ ብጡል (አባ ጠጣው)
10) ራስ አሉላ (አባ ነጋ)
11) ፊታውራሪ ብተ ጊዮጊስ (ባ ቻ)
12) ዋግሹም ጓንጉል ብሩ (አባ መርከብ)
ዘላለማዊ ክብር ታላቁን የዓድዋ ድል ላስመዘገቡ ኢትዮጵያዊያን ይሁን!
Learn about Limited-Time Offers, which give special bonuses that expire quickly, encouraging timely play.