አልጣሽ ብሔራዊ ፓርክ!
የአልጣሽ ብሔራዊ ፓርክ በድሮው አጠራር አላጥሽ በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በምዕራብ ጎንደር ዞን፤ ቋራ ወረዳ የሚገኝ ሲሆን ከ1930ቹ ጀምሮ ደን ከመሆን በዘለለ ጥብቅ ደን በመሆን በህብረተሰቡ ሲጠበቅ ቆይቷል፡፡
በርካታ ጥናቶች ከተካሄዱ በኋላ የአካባቢው ማህበረሰብ ፓርክ ይሁንልን ተደጋጋሚ ጥያቄ ታክሎበት በደንብ ቁጥር 38/1998 ብሔራዊ ፓርክ ሆኖ ታውጇል፡፡
በሰሜን-ምዕራብ አካባቢ የሚገኘውን የአገሪቱን ወካይ ቆላማ ስርዓተ-ምህዳርና በውስጡ በያዛቸው ብዝሀ-ህይወት ለመጠበቅ ታስቦ የተከለለ ፓርክ ነው፡፡
አልጣሽ ከ13.1 ዝቅተኛ እና 41.1 ከፍተኛ ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ የሙቀት መጠን ያስተናግዳል፡፡ በተለያዩ ወቅቶች የተለያየ እይታ ያለው ብሔራዊ ፓርክ በስተሰሜንና ምስራቅ የቋራ ወረዳ 7 ቀበሌዎች፤ በስተደቡብ የቤንሻጉል ጉምዝ ብሄራዊ ክልል (ብጃሚስ ብሔራዊ ፓርክን ጨምሮ) ወይም አይማ ወንዝ እና በስተምዕራብ ሱዳን (ዲንደር ፓርክ) ያዋስኑታል፡፡
በዚህም ብሔራዊ ፓርክ በብዝሀ-ሕይወት ሀብቱ በአገሪቱ ከፍተኛውን ድርሻ የሚይዝ ሲሆን ከእፅዋት ዝርያዎች 14 የቁጥቋጦ አ 57 ታላለቅ እፅዋቶች (የዛፍ አይነቶች)፤ ከ10 በላይ የሳር ዝርያዎች፣ 32 አጥቢ እንስሳት (በአፍሪካ ብቻ የሚገኝ የተባለለት እና በመጥፋት ላይ ያለ ባለ ጥቁር ጋማ የአንበሳ ዝርያን እና ዝሆንን ጨምሮ)፤ 8 አይነት ተሳቢና ተራማጅ እንስሳት ዝርያ፤ 16 የአይጥ ዝርያዎች፣ ሰጎንን ጨምሮ 240 የአእዋፍ ዝርያዎች፤ ከ16 በላይ የአሳ ዝርያዎች ይገኙበታል፡፡
የአልጣሽ ብሄራዊ ፓርክ የሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ ቆላማው አካባቢ በአረንጓዴ የደን ሽፋን ምክንያት የሰሃራ በረሃማነት መስፋፋትን ከሚከላከል ስነ-ምህዳር አካል ዋነኛ በመሆኑ አረንጓዴው መቀነት (Green Belt) ወይም አረንጓዴው ዘብ (Green Guard) ሚ ስያሜ ካታ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት የአልጣሽ ብሄራዊ ፓርክ የካርበን ልቀት ከመከላከል አንፃር አገሪቱ ካሏት ጥብቅ ቦታዎች እና ፓርኮች ሁሉ ከፍተኛውን ድርሻ ይይዛል፡፡
እ.ኤ.አ በ2012 የአለም አቀፍ አካባቢ ጥበቃ ተቋም ጥናት መሰረት የአልጣሽ ብሔራዊ ፓርክ 20,132,576 ቶን ካርበን አምቆ በመያዝ የዓለም አየር ንብረት ለውጥን ከመከላከል እንፃር የጎላ ድርሻ ያለው መሆኑን ያስርዳል፡፡
የአየር ንብረት ለውጥን ከመከላከል ብሔራዊ ፓርኩን ለየት ከሚያደርጉት ጉዳዮች የአፍሪካ ታላቁ አረንጓዴ ግድግዳ (Great Green Wall of Africa ) የፈጥ አል መሆኑ ው፡
#የጣና_ሃይቅና_ሌሎች_ውሃማ_አካላት_ልማትና_ጥበቃ_ኤጀንሲ
Узнайте о минимальном депозите на www.biz.if.ua.