ውቅር መስቀለ ክርስቶስ

ውቅር መስቀለ ክርስቶስ

የመስቀለ ክርስቶስ ውቅር ቤተ ክርስቲያን ከሰቆጣ ከተማ በስተምስራቅ አቅጣጫ 3 ኪ.ሜ ከተጓዙ በኋላ ከዋናው መንገድ ወደግራ በመታጠፍ አንድ ኪ.ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ ቤተ ክርስቲያኑ የሚገኝበት ስፍራ ልዩ ስሙ “ውቅር አባ ዮሐንስ” ይባላል፡፡ የመስቀለ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ከ495-525 ዓ.ም ባለው ዘመን ከአንድ አለት ተፈልፎሎ እንደተሰራ ይነገራል፡፡ የቤተ ክርስቲያኑ አሰራር ጥበብ ከላሊበላ ቤተ ክርስቲያን ጋር ተመሳሳይነት ያለው ነው፡፡ ከቤተ ክርስቲያኑ ውስጥ የተቆፈረ ጉድጓድ ያለ ሲሆን ከአንድ ሜትር ጥልቀት በኋላ ለሁለ አንደኛው ወደ ላሊበላ ሌላኛው ወደ አክሱም እንደሚያደርስ የሀይማኖት አባቶች ይናገራሉ፡፡ ቤተ ክርስቲያኑ በሦስቱም ጎኖቹ ከተፈለፈለበት ቋጥኝ ተለይቶ የቆመ ነው፡፡ በምዕራብ በኩል ግን ጣራው ከቋጥኙ ጋር ተያይዟል፡፡

ውቅር መስቀለ ክርስቶስ በክፍሎቹ በማራኪ ጥበብ የተቀረጹ 7 ክፍሎች፣ 4 በሮች፣ 5 ደረጃዎች፣ 14 ዝግ እና ክፍት መስኮቶች እንዲሁም 11 አምዶች ያሉት ጥንታዊ እና ማራኪ ፍልፍል ቤተ ክርስቲያን ነው፡፡ ፡፡ በህንጻው ግድግዳ ላይም በርካታ ጥንታዊ ስዕሎች ተስለውበታል፡፡ የአሳሳል ጥበቡ ጥንታዊውን ዘዴ የተከተለ ሲሆን ስዕሎች የተሰሩትም በጭቃና ግድግዳው ይ ጨርቅና በውቅር ህንፃው ላይ በተቀባ የኖራ ቀለም ላይ ነው፡፡ ጥንታዊ የብራና መጻሕፍት፣ የአፄ ካሌብና ከዋግ ሹሞች ጋር የተገናኙ ቅርሶች፣ በጥንታዊ ዘመን አስከሬንን አድርቆ የማስቀመጥ ጥበብ እንደነበራቸው የሚነገርላቸው ኢትዮጵያዊያን ምስክሮቻቸው በውቅር መስቀለ ክርስቶስ ለረጅም ዘመናት በቤተ ክርስቲያኑ ምዕራባዊ አቅጣጫ የተቀመጡት ቅሪት አካላት ይገኛሉ፡፡

ቤተ ክርስቲያኑ የአጼ ካሌብ እና የልጃቸው ገብረ መስቀል የክብር ዕቃ ማስቀመጫ እና የዋግ ሹሞች መቃብር እንደነበረም ይነገራል፡፡

Играйте в новые игры на www.biz.if.ua.

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top