የሰው ዘር ከአፍሪካ እንዴት ወደ ሌሎች አህጉሮች እንደሄደ የሚያሳይ ጥናት ይፋ ሆነ፡፡

የሰው ዘር ከአፍሪካ እንዴት ወደ ሌሎች አህጉሮች እንደሄደ የሚያሳይ ጥናት ይፋ ሆነ፡፡

በአማራ ክልል፣ በምዕራብ ጎንደር ዞን፣ በሽንፋ እና መተማ ረባዳ ቦታዎች ለ22 ዓመታት በተካሄደ ጥናትና ምርምር ጥንታዊ ሰው ከአፍሪካ ወደ ሌሎች አህጉሮች ደረቅ የአየር ንብረት ተቋቋሞ ወንዞችን እንደ መሻገሪያ በመጠቀም እንዴት እንደተጓዘ የሚያሳይ የጥናት ውጤት ይፋ ሁኗል፡፡ ጥናቱን የአዲስ አበባ እና ቴክሳስ ሂውስተን ዩንቨርሲቲ ምሁራን ያካሄዱት ሲሆን የጥናት ውጤቱን ያቀረቡት የምርምር ቡድን መሪው ዶ/ር ሙሉጌታ ፍሰሃ ናቸው፡፡

ዶ/ር ሙሉጌታ እንደገለጹት የጥናት ውጤቱ የሰው ልጅ ከአፍሪካ አህጉር ወደ ሌሎች አህጉራት መቼና እንዴት እንደተሻገረ እስካሁን ላልተመለሱ ጥያቄዎች ምላሽ የሰጠ ነው ብለዋል፡፡ ጥናቱ የተካሄደበት የሽንፋና መተማ ረባዳ ቦታዎች ይኑሩ የነበሩ ሰዎች የእሳተ ገሞራ የፈጠረውን የአየር ንብረት ጫና ለመቋቋም በኩሬዎች የሚያገኟቸውን ምግቦች ይጠቀሙ እንደነበርና በአካባቢያቸው የነበረው ምግብ ሲያልቅም ወንዝ እየተከተሉ ከቦታ ቦታ ይንቀሳቀሱ እንደነበረ መረጃው እንደሚያሳይ አብራርተዋል፡፡

በግኝቱ ጥንታዊ ሰው ከአፍሪካ ወደ ሌላ አህጉራት ለመሻገር በፊት ይታ ለምለም እና በዛፍ የተሸፈነ መሬት ተከትሎ ሳይሆን ደረቅ የአየር ንብረት ተቋቋሞ መሻገር እንደቻለና ይህ አዲስ እይታም የነበረዉን የምርምር አቅጣጫ ለማስፋትና የዓባይ ሸለቆ ተከትሎ ወደ ሜዲትራንያን ባህር የሚወስዱ ረባዳ ቦታዎች እና ወደ ሰሜን ምስራቅ ኢትዮጵያ የሚፈሱ ወንዞችና ረባዳ ቦታዎች አዳዲስ ምርምር እንዲካሄድባቸው የመነሻ ጥናት ይሆናል ተብሏል፡፡

የጥናት ውጤቱ ኢትዮጵያ የሰዉ ዘር መገኛ ብቻ ሳትሆን ዘመናዊ ሰው ለመጀመሪያ ጊዜ ሞቃታማ የአየር ንብረት ተቋቁሞ ከአፍሪካ ወደ ዓረቡ ዓለም እና ወደ አውሮፓ መሻገሩን የሚያሳይ የመጀመሪያ የሳይንስ ግኝት ካ ቅርስ ንትን ስ ተብሏል፡፡ የጥናቱ ውጤትም በመስኩ የመጀመሪያው የሳይንስ ግኝት በመሆን በNature የጥናት መጽሔት በዛሬው እለት ታትሟል፡፡

Ойын қауымдастығының мүшесі болу үшін Pin-Up Casino-да аккаунт ашып, ойынды тамашалаңыз.

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top