በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት በአማራ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሙሉዓለም የአማራ ባህል ማዕከል የኪነ-ጥበብ ሙያተኞችን ለማፍራት የሚያስችል ስልጠና እየሰጠ ነዉ፡፡
በማዕከሉ ትዉን ጥበባት ጥናትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት በሙዚቃም ሆነ በቴአትር ዘርፍ ተተኪ የኪነ-ጥበብ ከያኒያንን ለማፍራት የሚያስችል ክፍተት የለየና አቅማቸዉን ሊያጎለብት የሚችል ተግባራዊ ስልጠና ከሐምሌ 5/2016 ዓ.ም ጀምሮ ለአንድ ወር የሚቆይ ስልጠና በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡
ባህል ማዕከሉ ለሰልጣኞች የሚሠጣቸዉ የስልጠና ዘርፎች በትያትር ዘርፍ በጽህፈተ ተዉኔት፣ በትወና ሙያ እንዲሁም በሙዚቃ ዘርፍ በባህላዊ ዉዝዋዜ፣በድምጽ፣ በመሰረታዊ የሙዚቃ ፅንሰ ሀሳብ እና በባህላዊ የሙዚቃ መሳሪያ አጨዋወት በክራር፣ በማሲንቆና በኪቦርድ ስልጠና እየሰጠ ሲሆን በአጠቃላይ ከ250 በለይ ሰልጣኞች ስልጠናዉን በመዉሰድ ላይ ይገኛሉ:: በቀጣይ በምስራቅ አማራ ደሴ ከተማ እና በምዕራብ አማራ ጎንደር ከተማ ላይ ይህን ተተኪ የኪነ-ጥበብ ሙያተኞችን ለማፍራት የሚያስችል ስልጠና በቢሮዉ ጋር በመተባበር ለመስጠት ተዘጋጅተናል::
ኪነ-ጥበብን ለማሳደግ እና ተተኪ የኪነ-ጥበብ ሙያተኞችን ለማፍራት ስልጠና ወሳኝ ነው!!
ዛሬ የምንሰራዉ የነገ ታሪካችን ነዉ!!
1xbet 가입 시 첫 번째 베팅에 대한 특별 보너스를 놓치지 마세요. 이곳을 클릭하세요.